Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ላይ የተጣለ የኢኮኖሚ ማዕቀብ የለም

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ላይ የተጣለ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንደሌለ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ የ2014 ረቂቅ በጀት ላይ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡
አቶ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያ ከልማት አጋሮች ጋር ስላላት ግንኙት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ሃገሪቱ ከልማት ድርጅቶች ጋር ያላት ግንኙነት ከወቅታዊ ጫና በዘለለ ጤናማ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ጫናውም ጊዜያዊ በመሆኑ ይሻሻላል የሚል እምነት እንዳላቸው ነው ያብራሩት፡፡
ኢትዮጵያ በሁሉም ማዘናት ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት ያነሱት ሚኒስትሩ ይህንንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ከልማት ድርጅቶቹ ጋርም ያላት ግንኙነት የጠነከረ እና ለወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ብለዋል፡፡
ሃገሪቱም ላይም እስካሁን የተጣለ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንደሌለ ለምክር ቤቱ አባላት አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የልማት አጋሮች ከመሰረቱት ሃገራት አንዷ መሆንዋን አንስተውም እስካሁን ድረስም ከገንዘብ ፍሰት መዘግየት ውጪ አብዛኛው በፕሮጀክት መልክ የሚደረገው ፍሰት እንደቀጠለ አንስተዋል፡፡
የ2014 ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅም ምንአልባት የተወሰኑ የገንዘብ ፍሰቶች ቢዘገዩ ተብሎ የታመነባቸውን ፕሮግራሞች ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.