Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከ700 ሺህ ለሚበልጥ ህዝብ የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል 13 ወረዳዎች እና የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ከ700 ሺህ ለሚበልጥ ህዝብ የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ መሰጠቱ ተገለጸ።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ቃል አቀባይ ዶክተር አይዳ ሃይለስላሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በክልሉ ከትባቱ ለህዝቡ የተሰጠው ከሰኔ 5 ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ነው።

ክትባቱን ያገኙት በክልሉ 2 ሚሊየን ያህል ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከተያዘው እቅድ ውስጥ መሆኑን ገልጸው፥ ቀሪዎቹን ለማዳረስም በሚቀጥሉት ቀናት እንዲከተቡ ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻን ለማሳካት የጤና ሚኒስቴር ለክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ባለሙያዎችና የተለያዩ የመድሃኒቶችን ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በክረምቱ ወራት ለማካሄድ በተያዘው ሁለተኛው ዙር ክትባትም ለተጨማሪ 2 ሚሊየን ዜጎች ለመስጠት መታቀዱንም ዶክተር አይዳ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከሽሬ እንዳስላሴ እስከ ማይጨው ድረስ ባሉ መስመሮች ለ91 ሺህ ያህል ዜጎች ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት መሰጠቱንም አመላክተዋል።

ክትባቱን ላልወሰዱ ዜጎችም በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.