ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል የፈጸሙ የቀድሞ ባለስልጣናትን አሳልፋ ለመስጠት ተስማማች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል በመፈጸም የሚፈለጉ የቀድሞ ባለስልጣናትን ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ውሳኔው በቅርቡ በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተሰናባች ዓቃቤ ህግ ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጡ ማሳሰባቸውን ተከትሎ የተወሰነ ነው ተብሏል፡፡
ተላልፈው ከሚሰጡት የሀገሪቱ ባለስልጣናት መካከልም የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር አብደልራሂም መሃመድ አና የሃገር ውስጥ ሚኒስትር የነበሩት አህመድ ሃሩን ይገኙበታል፡፡
ውሳኔው በሀገሪቱ የካቢኔ አባላት በሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን÷በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ማምጣት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
ሱዳን ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ወንጀል የተከሰሱትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ለመስጠት ብትስማማም እስካሁን ግን ተፈጻሚ አልሆነም፡፡
በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2003 ላይ የተጀመረው የዳርፉር ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ካስከተሉ ግጭቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
በመንግስት ሃይሎች እና በአማጺያን መካከል በተደረገው በዚህ ጦርነት 300 ሺህ በላይ ዜጎች ሲገደሉ÷በሚሊየን የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
ምንጭ ÷ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡