ባለስልጣኑ የከተማዋን የብረት ፍሳሽ መስመር ክዳን ከፕላስቲክ በተሰራ ክዳን ሊቀይር ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከዚህ በፊት ይጠቀምበት የነበረውን የብረት የፍሳሽ መስመር ክዳን ከፕላስቲክ በተሰራ ክዳን ሊቀይር ነው፡፡
ለዚህም ባለስልጣኑ አለም አቀፍ ጨረታ በማውጣት በ20 ሚሊየን ብር ወጪ 4 ሺህ 800 ክዳኖችን ከህንድ ሀገር መረከቡን አስታውቋል፡፡
ከፕላስቲክ የተሰሩ ክዳኖችም እስከ 20 ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡
የፕላስቲክ ክዳኖቹ ከፍተኛ ጥንካሬ ያላቸው፣ ክብደታቸው ቀላል፣ የማይዝጉ እንዲሁም መልሶ ለመጠቀም የማይውሉና ለአገልግሎት ምቹ እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡
ባለስልጣኑ በፍሳሽ ማንሆል ክዳን ስርቆት በተደጋጋሚ ለከፋ ወጪ ሲዳረግ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን÷ ይህ ክዳን ችግሩን ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን