Fana: At a Speed of Life!

በአለርት ሆስፒታል የአዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢላል ሀበሺ የልማትና የመረዳጃ እድር እና አለርት ሆስፒታል በጋር በመሆን የአዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
ቢላል ሀበሺ የልማትና የመረዳጃ እድር በሱስና አደንዛዥ እጾች ተጠቃሚነት በወጣቱ ላይ እያስከተለ ያለውን የአእምሮ ጤና መታወክ ለመካላከል የማገገሚያ ማእከሉን ከአለርት ሆስፒታል ጋር በመሆን ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ አለምጸሃይ ፓውሎስ እንዳሉት በጋራ የሚሰራው ማዕከልም ለብዙ በሱስ ውስጥ ላሉ ዜጎቻችን ለመላቀቅና አምራች ዜጋ ለመሆን ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
አለርት ሆስፒታልም ያለውን አቅም ለመጠቀም መዘጋጀቱና በቅንጅት ለመስራት በተነሳሽነት መንቀሳቀሱ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ሀሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ በመተባበር እዚህ ያደረሱትን በሙሉ አመሰግነዋል።
ሁሉም ባለው በትብብርና በቅንጅት በመስራት ብዙ ወጣቶችን ከሱስ ተላቅቀው ሀገር እንዲገነቡ የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ወ/ሮ አለምጸሃይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ:- ጤና ሚንስቴር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+4
58,520
People Reached
1,458
Engagements
Boost Post
671
6 Comments
24 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.