Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የተረጋገጡ የመጨረሻ ውጤቶችን ይፋ በማድረግ ላይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሁሉንም ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን አስታወቀ።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት በምርጫ ህጉ መሰረት ጊዜያዊ ውጤቶችን ዛሬ ማጠናቀቅ ቢገባም በተለያዩ ምክንያቶች ያንን ማድረግ አልተቻለም ነው ያሉት።
ለዚህም የመደመር ሂደቶች አለመጠናቀቅ፣ በትራንስፖርት ችግር ወደማዕከል ውጤት ተጠቃሎ ያደረሰላቸው ክልሎች መኖር የሚጠቀሱ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ከዚያም ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ቅሬታዎችን ማቅረባቸውም ለመዘግየት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የገጠማቸውን ሁኔታ የገለጹ ሲሆን፥ በጋምቤላ አኮቦ የምርጫ ክልል ውጤቱ በሄሊኮፕተር የሚጓጓዝ መሆኑና በስፍራው ያለው የአየር ጠባይ ምምቹ ባለመሆኑ ውጤቱን መላክ አልተቻለም ብለዋል።
በአፋር ክልል ባሉ 7 የምርጫ ክልሎች እስካሁን ውጤት ተደምሮ አዲስ አበባ አልደረሰም ነው ያሉት።
በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ አራት የምርጫ ክልሎች፣ በአማራ ሦስት የምርጫ ክልሎች ውጤት ማሳወቅ አልተቻለም ነው ያሉት።
በአሁኑ ሰዓት ወይዘሪት ብርቱካን በቦርዱ የተረጋገጡ የመጨረሻ ውጤቶችን ይፋ በማድረግ ላይ ናቸው።
በአማራ ክልል 3 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል አልደረሱም።
በኦሮሚያ ክልል የ4 ምርጫ ክልሎች ውጤትም አልተጠናቀቀም።
በደቡብ ክልል የአማሮ ኬሌ እና የአርባ ምንጭ የምርጫ ክልሎች ውጤት አልደረሰም።
በሌላ በኩል በፓርቲዎች ቅሬታ የተነሳባቸው ምርጫ ክልሎች ውጤት ዛሬ ይፋ ያልተደረገው÷በሚያነሱት የፓርቲዎች ጥያቄ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያሳድር በሚል ውጤታቸው አልተገለጸም ብለዋል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ የ73 የምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል ቦርዱ በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ የምርጫ ክልል አንድ እጩ ስምና ምልክታቸው ባለመኖሩ ምርጫው እንዲቆም መወሰኑ አይዘነጋም።
ሆኖም ያስተላለፍነው መልዕክት በተለያዩ ምክንያቶች በመዘግየቱ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ አርብቶ አደር በመሆኑ፣ ስሜ አልተካተተም ብለው የነበረው ግለሰብ በመልካም ፈቃዳቸው የተሰጠው ድምፅ እንዲያዝ በማለታቸው፣ ከ139 ምርጫ ጣቢያዎች 105 ያህሉ ድምፅ በማስጠታቸው፣ ጳጉሜ 1 ህብረተሰቡ ባለው አኗኗር ምክንያት ሊገኙ የማይችሉ በመሆናቸው የተሰጠው ድምፅ እንዲያዝ፣ ድምፅ ባልተሰጠባቸውም በአጭር ቀን እንዲሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
ምስክር ስናፍቅና አፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
172,774
People Reached
14,581
Engagements
Boost Post
2.3K
59 Comments
128 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.