Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዩ ወር የሚከሰተው እርጥበታማ አየር ለውሃ ሀብት መጨመር አስተዋፅኦ ሊኖረው ይችላል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዩ ወር የሚከሰተው እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለውሃ ሀብት መጨመር አስተዋፅኦ ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ÷ የአየር ትንበያ ሁኔታ እንደሚያሳየው በቀጣዩ ወር የሚከሰተው እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ለተፋሰሶች መጨመር አስተዋጽኦ ቢኖረውም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚከሰተው ከባድ ዝናብ በገደላማ ቦታዎች መሬት መንሸራተትና ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል፡፡
ለዚህም ጥንቃቄ ያስፈልጋል ነው ያለው፡፡
በዚህም ወቅታዊውን የእርጥበት መጠን በመደበኛ ማግኘት የጀመሩት የምዕራብ አጋማሽ የሃገሪቱ ተፋሰሶች የተሻለ የእርጥበት ሁኔታ ሊኖራቸው እንደሚችል ትንበያ አስቀምጧል፡፡
በሰሜን ምስራቅና የምስራቅ ተፋሰሶችም ተመሳሳይ የአየር ፀባይ እንደሚኖራቸውም ነው የተተነበየው፡፡
ይህን ተከትሎም በአብዛኛው አባይ፣ ባሮ አኮቦ፣ ተከዜ፣ ስምጥሸለቆ፣ ኦሞጊቤ እንዲሁም አዋሽ ተፋሰሶች ከፍተኛና በጣም ከፍተኛ እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ይጠበቃል፡፡
በአንዳንድ የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ደግሞ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል ያለው ኤጀንሲው የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባም አስጠንቅቋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.