አቶ እርስቱ ይርዳው በክልሉ ምንም መሬት ሳይታረስ እንዳይቀር አሳሰቡ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በክልሉ ምንም መሬት ሳይታረስ እንዳይቀር አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ምክር ቤት የ5ኛ ዙር 6ኛ አመት መደበኛ ጉባዔ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸው በኢትዮጵያ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በደቡብ ክልል ያለውን መሬት በአግባቡ ተጠቅሞ ለሀገር አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርብናል ያሉ ሲሆን የክልሉ መንግስትም ለግብርና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማቅረብ ከክልልና ከፌዴራል ግብዓት አቅራቢዎች ጋር እየሰራ ነው ብለዋል ።
በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በኩልም የመሬት ጥናት መካሄዱን ገልፀው በኩታ ገጠም የሚለሙ፣ በአነስተኛ ዝናብ የሚለሙና በመስኖ የሚለሙ መሬቶች ተለይተዋል ነው ያሉት።
አርሶአደሩም መሬቱን በጊዜው አርሶ በቂ ምርት ማምረት እንዲችል በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎችና የመንግስት አመራሮች እገዛ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!