ምክር ቤቱ ተጨማሪ ሹመት አፀደቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት በተጓደለው የቢሮ ሀላፊ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በእጩነት የቀረቡትን አቶ ቢረጋ ብርሃኑን ሹመት አፅድቋል።
በዚህም አቶ ቢረጋ ብርሃኑ የደቡብ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።
አቶ ቢረጋ ብርሃኑ ከዞን ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ በተለያዩ የአመራርና በባለሙያነት ያገለገሉ መሆናቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
አቶ ቢረጋ ብርሃኑም የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!