Fana: At a Speed of Life!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተመሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ3 ሺህ በላይ አዲስ ተመሪዎችን መቀበል ጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ እና ነገ ተማሪዎችን እንደሚቀበልም አስታውቋል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ ለፋና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ አቀባበል ብሎም በቀጣይ ቀናት ለሚኖረው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ከዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች፣ ከሰራተኞች፣ ከተማሪ ህብረት አባላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከነዋሪዎች የተውጣጣ ኮሚቴ አዋቅሮ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ከገቡ በኋላም የኮቪድ 19 ፕሮቶኮልን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ፣የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ የትምህርት ቀናትም በኮቪድ ምክንያት ዘግይቶ የቆየውን የመማር ማስተማር ስራ ማካካስ በሚያስችል መልኩ የመማር ማስተማር ስራው እንደሚካሄድና ለዚህም ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.