Fana: At a Speed of Life!

የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዚህም የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባርን ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበርና በኢትዮጵያ መካከል ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል የተፈረሙ አራት የብድር ስምምነቶችን ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተርና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር የተስማማችባቸውን ሁለት የመንገድ ደህንነት ቻርተሮችንም አፅድቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.