Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከተማሪዎች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከተማሪዎች ጋር በመሆን በጉለሌ እጽዋት ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል።
“የሀገር ተረካቢነታችንን በአረንጓዴ አሻራችን ኢትዮጵያንችንን እናልብስ” በሚል ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ማህበረሰብ አመራሮች ችግኞችን ተክለዋል።
ተማሪ እያለን ሰኔ 30 ዓመቱን ሙሉ የተማርነውን ውጤት ለማወቅ በጉጉት የምንጠብቀው ቀን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ዛሬ ደግሞ ተማሪዎች ኢትዮጵያን እናልብሳት በማለት ችግኝ በመትከል አሻራ ማኖራቸውን ገልጸዋል።
ዛሬ የተተከሉ ችግኞችም ለነገይቱ ኢትዮጵያ እንዲሁም አዲስ አበባ ልምላሜ የተላበሰች ፣ ለኑሮ የተመቸች እንድትሆን የሚያደርግ በመሆኑ ተማሪዎች ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ሲሉ ምክትል ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በከተማዋ በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ከ100ሺህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምሀርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕረስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.