ኢራን ዩራኒየም ማበልጸግ ጀመረች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ኒውክሌር ማምረት የሚያስችላትን ዩራኒየም ሜታል ማበልጸግ መጀመሯን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አቶሚክ ክትትል አስታወቀ፡፡
ኢራን ለኃይል ማመንጫነት ለማዋል ዩራኒየም እያበለጸገች እንደምትገኝ ለዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ማስታወቋም ተሰምቷል፡፡
ይህንን ተከትሎም ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን የኢራን አካሄድ ከዚህ ቀደም የተቋረጠውን የ2015 የኒውክሌር ስምምነት ዳግም ወደ ጠረጴዛ ለመመለስ አዳጋች እንደሚሆን ነው ያስታወቁት፡፡
የተቋረጠውንም ስምምነት ለማስቀጠል ከሚያዝያ ጀምሮ በቬይና ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
አሜሪካ በበኩላ የኢራንን አካሄድ በመኮነን ጉዳዮችን ወደ ኃላ የሚመልስ ነው ብላለች፡፡
የጆ ባይደን አስተዳደርም በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም የተጣለውን ማዕቀብ ያለማንሳቱ ተገልጿል፡፡
የኢራን አዲሱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ በበኩላቸው÷ስምምነቱን ለመተግበር አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታነሳ ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
See Translation

144
5 Comments
10 Shares
Like
Comment
Share