በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተናን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በአረንጓዴ አሻራ የማሳራፍ ፕሮግራመሙ እያንዳንዱ ተማሪ 12 ችግኞችን በነፍስ ወከፍ የተከለ ሲሆን፥ በወረዳው ያሉ 26 ሺህ ተማሪዎች በጠቅላላው 3 መቶ ሺህ ችግኞችን እንደሚተክሉ በያሊ ትምህርት ቤት በነበረው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል።
የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ማቲዎስ ቄይሳም፥ የነገ ሃገር ተረካቢዎች ኢትዮጵያን የማልበስ ሂደቱ ላይ ብርቱ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
በተለይም በትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ የሚተከሉ ችግኞች ስነምህዳርን ከማስተካከል ባሻገር ፍራፍሬዎች የትምህርት ቤቶችን የውስጥ ገቢ ከፍ እንደሚያደርጉም ነው የገለፁት።
ተተኪ ተማሪዎች የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አደራ ተጥሎባቸዋል ነው የተባለው።
በሰሜን ቤንች ወረዳ በዚህ ክረምት 13 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተጠናቋል።
በፍሬው አለማየሁ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!