ጅቡቲና ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን መዘግየት ለመቅረፍ ተስማሙ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲና ኢትዮጵያ መንግስት የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን መዘግየት ለመቅረፍ ተስማምተዋል፡፡
የኢትዮ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የውጪ ንግድ ፎረም በሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልዕክተኛ ምክትል ኃላፊ፣ የሁለቱ ሀገራት ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንቶች፣ የዶራሌ ሁለ ገብ ወደብ ስራ አስኪያጅ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበር ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
በፎረሙ ኢትዮጵያ ለውጪ ንግድ የምታቀርበውን የቁም ከብት ከቀድሞው በተሻለ ፍጥነት ለማስተላለፍ አበክራ እንደምትሰራ ጅቡቲ ገልጻለች፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ላኪዎች በንግዱ የሚያጋጥሟቸውን መጠነ ሰፊ ተግዳሮቶች አንስተዋል፡፡
በተሰጠው ምላሽም ኢትዮጵያና ጅቡቲ በሚኖራቸው ቀጣይ የንግድ ትስስር ሲስተዋሉ የነበሩ መጉላላቶች እንደሚቀረፉና በቀጣይ በዘርፉ አዳዲስ የማሻሻያ ስራዎች እንደሚሰሩ ቃል ተገብቷል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው ፎረም ማጠናቀቂያ ላይ የቁም እንስሳት ንግዱን በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የዶራሌ ሁለ ገብ ወደብ በተሳታፊዎች ተጎብኝቷል፡፡
በውይይቱ መጨረሻም ባለድርሻ አካላቱን ያካተተ የመፍትሄ ሃሳብ ስትራቴጂክ ዕቅድ የሚያቀርብ ኮሚቴ መሰየሙን ከኢትዮጵ ብሮድካስት በለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!