በጅማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጥሯል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለፀ።
በዞኑ ለ53 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ነው ለ65 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የተቻለው፡፡
ወጣቶቹ በ7 ሺህ ማህበራት ተደራጅተው በግብርና፣ በንግድ፣ በእንጨትና ብረታብረት ሥራዎች መሰማራታቸውን የጅማ ዞን ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤሊያስ መሃመድ ገልፀዋል፡፡
ከስራ እድል ፈጠራው 67 በመቶ ግብርና መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው÷ በ52 ሚሊየን ብር 32 ትራክተሮች ተገዝተው ለወጣቶች መሰጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የዳቦ መጋገሪያ፣ እንጨት መሰጠንቅያ፣ የልብስ መስፊያና የጎሚስታ ማሽኖች በ10 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ተገዝተው ለወጣቶቹ በብድር ተላልፈዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዞኑ ለስራ እድል ፈጠራ 2 13 ሚሊየን ብር ብድር ለመስጠት ታቅዶ 1 21 ሚሊየን ብር ለወጣቶቹ መሰጠቱ ተገልጿል።
የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል 30 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል፡፡
በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!