አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፖላንድ ፕሬዚዳንት አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን የሹመት ደብዳቤያቸውንለፖላንድ ፕሬዚዳንት ለአንድርዘጅ ዱዳ አቅርበዋል።
አምባሳደሯ ተቀማጭነታቸው በጀርመን፣ በርሊን አድርገው በፖላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት።
በወቅቱም በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሰበብአዊ ዕርደታ ተደራሽነት እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት መንግስት የወሰዳቸው እርምጃዎች ዙሪያ አምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!