Fana: At a Speed of Life!

በበጋው ወቅት የእሳት አደጋ በደረሰበት የወፍ ዋሻ ደን ችግኝ ተተከለ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ሰራተኞች በበጋው ወቅት የእሳት አደጋ በደረሰበት የወፍ ዋሻ ደን ችግኝ ተከሉ።
የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው÷ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ በወፍ ዋሻ ደን የተካሄደውን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስጀምረዋል።
ሚኒስትሯ የዛሬው ችግኝ ተከላ በበጋው ወቅት ቃጠሎ በደረሰባችው ጥብቅ ደኖች ላይ ችግኝ ለመትከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የያዘው መርሀ ግብር አካል ነው ብለዋል።
በዝቋላ፣በአሰቦትና በየረር ጥብቅ ደኖች ላይ ተመሳሳይ ችግኝ ተከላ ይከናወናል ያሉት ዶክተር ሒሩት ÷ በቃጠሎ የተጎዱ ደኖች ላይ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ የአካባቢው ማህበረሰብ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ስፖርት ኮሚሽን፣ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን፣ቱሪዝም ኮሚሽንና የብሔራዊ ቴአትር ባለሙያዎችና አመራሮች ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.