Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ ጃፓን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቶኪዮ ማወጇ ተሰማ፡፡

አዋጁ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ፍፃሜውን እስከሚያገኝ ድረስም ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ እንደገለፁት፣ አዋጁ ከፈረንጆች ሐምሌ 12 ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ነሐሴ 22 ድረስ የፀና ይሆናል፡፡

አዋጁ ስራ ላይ ሲውልም ባርና ሬስቶራንቶች የአልኮል መጠጦችን መሸጥ እንደማይችሉ የተገለፀ ሲሆን፣ የሚዘጉበት የሰዓት ገደብም እንደተቀመጠ ነው የተመላከተው፡፡

ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መውጣት በምክንያትነት የተገለፀው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ከተካሄደ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንደሆነ ነው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.