በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኞ ጀምሮ ይሰጣል
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሀምሌ 5 እስከ ሀምሌ7 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡
በትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ተቋማት ግንባታ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀሰበላ አዜን እንደገለፁት ÷በአብዛኛው የክልሉ ቦታዎች ፈተናው ተሰራጭቷል፡፡
በፈተናው ወቅትም ተማሪዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን መፈተን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ምክትል የቢሮ ሃላፊው ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!