Fana: At a Speed of Life!

ትልቋና መልከ ብዙዋን ኢትዮጵያ ለማገልገል የተለያዩ ፈተናዎችን አልፈን እዚህ ደርሰናል- ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በምርጫው ሂደት ላይ የቦርዱ አመራር አባላት የጥያቄና መልስ መርሃግብር እየተካሄደ ነው።
አባላቱ በሀገርበቀል ታዛቢ ሲቪክ ማህበራትን ለማሳተፍ፣ ምርጫውን ገለልተኛ ተዓማኒ ለማድረግ፣ በአዲስ የሰው ሀይል ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ቦርዱን መልሶ የማዋቀር፣ ልምድና እውቀቶችን በማዋሃድ ቀድመው ችግር ሆነው ነበር ያሉት የቦርዱ አመራሮች÷ አዲስ ልምድ ያገኙበት እንደሆነ ገልፀዋል።
በዚህም ቦርድ አምስት አገራዊ ምርጫዎች፣ ሁለት የአካባቢ ምርጫና ስድስት ሕዝበ ውሳኔዎችን ከዚህ ቀደም ማደራጀቱ ተገልጿል።
እንደአዲስ መዋቀሩም ተመላክቷል። ይህም ከሰው እስከ መስሪያ ቤት የደረሰ ነው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አብረዋት ከሰሩት አዳዲስ ልምዶች ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
“ከቀልድ አዋቂው ውብሸት አየለ፣ ከቀድሞ መምህሬ ዶክተር አበራ ደገፉ ጋር የሰራሁበት ትልቅ ሀላፊነት ነው” ብለዋል።
ትልቋና መልከ ብዙዋን ኢትዮጵያ ለማገልገል የተለያዩ ፈተናዎችን አልፈን እዚህ ደርሰናል ሲሉም ወይዘሪት ብርቱካን ተናግረዋል።
በአፈወርቅ እያዩና ሀቢብ መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.