ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረው የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፉላቸው የከተማው ካቢኔ ወሰነ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ቀደም ሲል የነበረው ካቢኔ በወሰነው መሰረት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወሰኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል ።
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2009 ዓ.ም ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ቀደም ሲል የነበረው ካቢኔ በወሰነው መሰረት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው ወሰኗል።
በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ለተለያዩ ተቋማት የተላለፉ የ40/60 እና 20/80 ቤቶችም የከተማ አስተዳደሩ ካለበት ከፍተኛ የወለድ ጫና ለማዳን ተቋማቱ ሙሉ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ እንዲተላለፉ ውሳኔ ማሳለፉን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!


0
People Reached
310
Engagements
Boost Post
281
9 Comments
20 Shares
Like
Comment
Share