Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወደኋላ የማይመለስ ተቋምን መመስረት ችሏል-ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወደኋላ የማይመለስ ተቋምን መመስረት ችሏል አሉ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ።

ከዚህ መካከል የሚታይ ገለልተኝነት መስራቱ ነው ብለዋል።

ምርጫው እንደሀገር የተማርንበት ነው ሲሉ ወይዘሪት ብርቱካን ጨምረዋል።

ግልፅነትና ተጠያቂነትንም ተግብሯል ነው ያሉት።

ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 150 ሺህ ሰራተኞች አሰልጥነን አሰማርተናል ነው ያሉት ሰብሳቢዋ።

ዜጎች በንቃት በትዕግስት በምርጫው ላይ የሳተፋቸው ዜጎች በቦርዱ ላይ ያላቸውን እምነት ያሳየ እንደሆነም አስረድተዋል።

በስጋት ውስጥ ቢሆንም በሰላም መካሄዱ የፀጥታ ሀይሎች ከህዝቡ አመኔታ ጋር ተደምሮ የመጣ ነውም ብለዋል።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እኩል ሁሉንም ከማየት አንፃር ክፍተቶች መኖራቸውን ወይዘሪት ብርቱካን ገልፀዋል።

የምንግስት ሚዲያዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በቂ ሽፋን አልሰጡም፣ ለመንግስት ባለስልጣናት የሰጡትን ያህል ለሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በቂ የአየር ሽፋን አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡

ለዜጎች ወሳኝነት ያለው የአካባቢ ምርጫም በቀጣዩ አመት እንደሚካድ ነው የገለፁት።

የሰራነውን ሁሉ የመሰነድና ታሪክን የማኖር ስራም እንደሚሰራ አንስተዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.