የኮቪድ19 መከላከያ ቁሳቁሶች ወደ ኢትዮጵያ ተልከዋል
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳያስፖራው ማህበረሰብ የተበረከቱ የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶች ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ ጽፈዋል።
በኢትዮጵያ ኮቪድ 19ን ለመከላከል በዳያስፖራ ወገኖች ኤምባሲያችን ድረስ የተላኩልንን የመከላከያ ቁሳቁሶች ወደ ኢትዮጵያ ልከናል ያሉት አምባሳደር ፍጹም ÷ ለለገሱ ፣በማጓጓዝ ለተባበሩት ለኢትዮጵያ አየር መንገድና ለናታን ትራቭል ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!