በኢትዮጵያ የጡት ማጥባት ምጣኔው አበረታች ቢሆንም ሳይንሱ በሚያዘው መንገድ ማጥባት ላይ ክፍተት እንዳለ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጡት ማጥባት ሳምንት ከሐምሌ 25 እስከ ነሀሴ 1 “ጡት ማጥባትን መጠበቅ የጋራ ኃላፊነት ነው” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።
ይህንኑ አስመልክቶ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መገለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው በሀገሪቱ ጡት የሚያጠቡ እናቶች 97 በመቶ ያህል ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ ይህም አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።
ሆኖም ሳይንሱ በሚያዘው መንገድ ማጥባት ላይ ግን አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩን ኢቢሲ ዘግቧል።
በዚህ የጡት ማጥባት ሳምንትም ግንዛቤውን በማህበረሰብ ደረጃ ማስፋትና ለሚያጠቡ እናቶች ምቹ ሁኔታን መፍጠር ላይ የመስራትን አስፈላጊነት ማጉላት ይገባል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!