Fana: At a Speed of Life!

ጁንታው ወጣቶቻችን በስናይፐር ገድሎብናልና ይህን ተግባሩን እንዲደግም አንፈቅድም – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጁንታው ወጣቶቻችን በስናይፐር ገድሎብናል፤ ዘርፎናል፤ ከፋፍሎናልና ይህንን ተግባሩን እንዲደግም አንፈቅድም ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡

በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ንግግራቸውን ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ ጁንታው በመቶ ሰዎች ወንበር ላይ ብቻውን ሲቀመጥ ነበር ያሉ ሲሆን÷ አሁን የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ወንበር እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ከተቀበረበት እንዳይነሳ አድረገን እንቀብረዋለን ሲሉም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

በአንድ በኩል ልማት በሌላ በኩል ጁናታውን መመከት ላይ ልታተኩሩ ይገባል ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ኢትዮጵያዊያነት ደማችን ውስጥ ያለ መሆኑን በዚህ መድረክ አይተነዋል ብለዋል፡፡

ለጁንታ የምትላላኩ ሀይሎች ኢትዮጵያ እንደፈላጋችሁ ማድረግ አትችሉም፣አይሳካላችሁም ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.