Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ የኬንያ የፓርላማ አባላትን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ በጅግጅጋ የሚገኘውን የኬንያ የፓርላማ አባላት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለኬንያ ፓርላማ አባላት በሶማሊ ክልል ባለፉት ሶስት አመታት የተከወኑ የልማት ሥራዎች በተለይ በሰላምና ደህንነት፣ በጤና፣ በመንገድ በትምህርት እንዲሁም በአጠቃላይ የክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል።

የለውጥ አመራሩ ክልሉን መምራት ከጀመረ በኋላ በተለያዩ ሴክተሮች ትላልቅ ለውጦች መመዝገባቸውንም አስረድተዋል፡፡

በተለይ በክልሉ የፖለቲካ ምህዳሩ እንደሰፋና ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ መቻሉንም ነው የገለፁት፡፡

ማንም በአመለካከቱ እንደማይታሰርና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፈፀሙባቸው የነበሩ ቦታዎች መዘጋታቸውንም ለልዑኩ ተናግረዋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ በበኩላቸው በተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃና እንደተደሰቱ ገልፀው ልምዳቸውን አካፍለው ባለፉት 27 አመታት ስለ ሶማሊ ክልል ችግሮችና መፈናቀሎችን ይሰሙ እንደነበረና ለመምጣትም ያስፈራ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡

አሁን ላይም ዘርፈ ብዙ ለውጦች እንደተመዘገቡ መታዘባቸውን ገልፀዋል፡፡

ከክልሉ ጥሩ ልምድ እንዳገኙ በመግለፅ ወደ ተመረጡበት የኬንያ ክልሎች ሲመለሱ ያዩትን ነገር እንደሚያካፍሉ መግለጻቸውን የሶማሊ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.