Fana: At a Speed of Life!

በሞረትና ጅሩ ወረዳ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ጅሁር ኮሲያንባ ቀበሌ ቦንብ ፈንድቶ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ፡፡
በቀበሌው ሰርጠሶስ በሚባል መጠጥ ቤት ውስጥ በፈነዳ ቦምብ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሰባት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ መሆኑን የጅሁር ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ዘነበ ሰሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በዚህ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አራት ሰዎች ደብረ ብርሀን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የቦምብ አደጋው የደረሰው ቤት ውስጥ ነው ያሉት ኮማንደር ዘነበ አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ ማን እንደሆነ በማጣራት ላይ ነን ብለዋል።
በአላዩ ገረመው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.