Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በመተከል ነዋሪዎች ላይ የፈጠረውን የመለያየት ሴራ በአንድነት ማክሸፍ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ በመተከል ነዋሪዎች መካከል የፈጠረውን የመለያየትና የመጠራጠር ሴራ አንድነት በመፍጠር ማክሸፍ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።
 
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በዞኑ አስተማማኝ ሰላም መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዞኑ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ወጣቶች የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት በክልሉና በዞኑ ሰላም እንዳይፈጠር በስልጣን ማጣትና በሌሎች ምክንያቶች ያኮረፉ ግለሰቦችን መቐለ ድረስ ወስዶ በማሰልጠን ለጥፋት ማሰማራቱን ዋና አስተዳዳሪው አንስተዋል፡፡
 
እነዚህ የጥፋት ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃትም በርካቶች ለህልፈት እና ለመፈናቀል ተዳርገዋል ነው ያሉት፡፡
 
አሸባሪው ሃይል የአካባቢውን ህዝብ በቀለም ፣ በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈልና መጠራጠርን በመፍጠር የህዳሴውን ግድብ ስራ ለማስተጓጎል አበክሮ መስራቱን ያስታወሱት አቶ ጋሹ÷ በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በከፈለው ዘርፈ ብዙ መስዋዕትነት የግድቡ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በወቅቱ ሊከናወን መቻሉን ገልጸዋል።
 
የህዳሴ ግድብ ቀጠናን ሰላም ለማረጋገጥ ከየወረዳው እና አጎራባች ክልሎች የተውጣጡ ሚሊሻና ምልሶችን በማሰልጠን የማስታጠቅ ስራ በትኩረት እና በፍጥነት እየተሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል ፡፡
 
ህወሓት በዞኑ በርካታ ተላላኪዎቹን አሹልኮ የማስገባት ሙከራዎችን በማድረግ ላይ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን÷ ነዋሪዎች አንድነታቸውን በማጠናከር የጠላትን ሴራ ማክሸፍ እንደሚኖርባቸውም ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የየበኩላቸውን ለማበርከት ቃል መግባታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.