Fana: At a Speed of Life!

ስምንት የአሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ስምንት የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል በሰጡት መግለጫ፥ ህወሓት ኢትዮጵያዊነት እንዲዳከም ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ብለዋል።
አሁን ደግሞ እየፈፀመ ያለውን ግልፅ ወረራ ለመመከት የደሴ ከተማ የተለያዩ ግብረ ኃይሎችን በማቋቋም አሽባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ ወደ ስራ ተገብቷልም ነው ያሉት።
የአካባቢው ሰላምና ደህንነት ከሰርጎ ገቦች በመጠበቅ በኬላ ፍተሻ በተለያዩ ቦታዎች አሰሳ ተደርጎ 354 ተጠርጣሪዎች ተይዘው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ያሉት ከንቲባው÷ ስምንት የሚሆኑት ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው ብለዋል።
የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግም የተለያዩ መሳሪያዎች መያዛቸውን አንስተው፥ ሁሉም የፀጥታ ሀይሎች ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት በቀን እና ሌሊት አካባቢያቸውን እየጠበቁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ወደ ከተማው 100 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች መጥተዋል ያሉት ከንቲባው፥ የደሴ ከተማ ህዝብ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የእርዳታ ድርጅቶችም ወደ ከተማው በመምጣት ለተፈናቃዮች ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.