Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የልምድ ልውውጥ መድረክ በጅንካ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተመረጡ ሆስፒታሎች፣ የደቡብ ኦሞ ዞን አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
በውይይት መድረኩ በተነሳሽ፣ብቁና ርህራሄን በተላበሰ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ምክክርና የልምድ ልውውጥ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሰግድ እንዳሉት በጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ሆስፒታሎች መስፋፋት ይኖርባቸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.