Fana: At a Speed of Life!

በቡታጅራ ከተማ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሰላማዊ ሰዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ እንዲሁም ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
ሀገርን ከጥፋት ሀይሎች ለመታደግና ለሉዓለዊነታችን የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው መከላከያ ሰራዊት እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር፣ የመስቃንና የምስራቅ መስቃን ወረዳና አጠቃላይ የዞኑ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
በሰልፉ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ለማን ሌሎች አመራሮች መገኘታቸውን የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.