Fana: At a Speed of Life!

በዳባት ከተማ ሰርጎ ገብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ ሰርገው ለመግባት የሞከሩ የአሸባሪው ህወሓት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
ወደ ዳባት ከተማ ለመግባት የሞከሩ 150 ሰርጎ ገቦችን በመያዝ በተደረገ የማጣራት ሂደት 17ቱ ከሽብር ቡድኑ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ሳይኖራቸው እንዳልቀረ የዳባት ከተማ ከንቲባ አቶ ክብር አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል፡፡
እነዚሁ ተጠርጣሪዎችም በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል፡፡
የከተማዋ ወጣቶች የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ወደ ከተማዋ ሰርገው እንዳይገቡ በፍተሻ ስፍራዎች በንቃት በመሳተፋቸው እስካሁን በከተማዋ ምንም ችግር እንዳይፈጠር ማስቻሉን ከንቲባው ተናግረዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በሀሰት የዳባት ከተማን እንደያዘ አድርጎ ቢያስነግርም ከተማዋ በሙሉ ሰላም ላይ እንደምትገኝም ነው የተናገሩት፡፡
የከተማው ወጣቶች እያደረጉት ያለውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በክብረወሰን ኑሩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.