አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ዘርፉን ያዘምናል
አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ፍኖተ ካርታ የትምህርት ጥራትንን የሚያረጋግጥ፣ የትምህርት ስርዓቱ ከኢኮኖሚው ጋር እንዲጣጣምና ዘርፉ በቴክኖሎጂ እንዲዘምን የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ከዚህ ቀደም በነበረው ስርዓተ ትምህርት ላይ የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ እና በጥናት ላይ የተመሰረተ ፣ የአገሪቱን የልማት ጥያቄ ሊመልስ እንደሚችልም መረጃው ጠቁሟል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ እንደሚያመለክተው በተጠናቀቀው የትምህርት ልማት ዘርፍ በትምህርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት በትምህርት ቤት ማሻሻል ፣ በትምህርት ልማትና የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ፣ በዲጂታል ትምህርት ቴክኖሎጂ እና በሌሎችም በርካታ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል።
የትምህርት ስራን ለማሳደግ በየደረጃው ብቃት ያለው አመራር መፍጠርና ማልማት ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።
የጎልማሶች ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅበጎልማሶች ትምህርት ከ524ሺህ የሚበልጡ ጎልማሶች የብርሃን ምዘና ፈተና አልፈው የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።
ከ322 ሺህ ለሚበልጡ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና መሰጠቱ በ2013 ከተከናወኑ በርካታ ስራዎች መካከል የሚጠቀስ መሆኑንም መረጃው ጠቁሟል።
በአንፃሩ የህወሃት አሸባሪ ቡድን በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በከፈተው ጦርነት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ዉጪ መሆናቸውና በርካታ ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ነው የተገለጸው።
“ጥራት ያለውን ትምህርት እንማራለን፣ እናስተምራለን፣ ለሁሉም ዜጎቻችን በማዳረስ ኢትዮጵያችንን እናበለፅጋለን!” በሚል መሪ ቃል የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የክልል ቢሮ ሃላፊዎች፣የትምህርት ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ዓመታዊ የትምህርት ጉባኤ መካሄዱ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!