Fana: At a Speed of Life!

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ያሳተመውን መዝገበ ቃላትና የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ አስር ቋንቋዎችና ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ያሳተመውን መዝገበ ቃላትና የሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡
ሀገር በቀል እሴቶችን ከጥፋት ለመታደግ የተለያዩ ምርምሮች እየተከናወኑ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ ተናግረዋል፡፡
ከምርምሮቹም መካከል የሀገሪቱን ቋንቋና ባህልን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲቻል ሀድይሳ፣ ከንባቲሳ፣ ሲዳምኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ኑዌርን ጨምሮ በአስር ቋንቋዎች መዝገበ ቃላትና የሞባይል መተግበሪያ ማዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.