Fana: At a Speed of Life!

የሚበጀንን ለመምረጥ የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው- የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በነቂስ በመውጣት በወሰደው የምርጫ ካርድ የሚበጀውን መምረጥና ዲሞክራሲያዊ መብቱን መጠቀም እዳለበት የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቁ ያሉ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ እንደገለፁት÷ መስከረም 20 በሚካሄደው ምርጫ ለመምረጥ ዝግጁ ናቸው፡፡
ህዝቡም በእለቱ ለሀገር የሚበጀውን ፓርቲ በመምረጥ የሀገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲጎለብት ሚናውን መወጣት ይገባልዋል ብለዋል፡፡
ከሁሉም የሀገር ሰላም እንደሚበልጥ በመረዳት÷ በተለይም ወጣቶች ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
መላው ህዝብም የአካባቢውን ሰላም በንቃት በመጠበቅ እና የምርጫውን ውጤት በፀጋ በመቀበል ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.