Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ መታወቂያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የብሔራዊ መታወቂያ ለሰላም፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት፣ ለሀገር ደህንነት መልከ ብዙና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ።
የብሄራዊ መታወቂያ ትግበራ ዝግጅት የደረሰበት ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በሰላም ሚኒስቴር መሪነት በሚመለከታቸው ተቋማት የጋራ ተሳትፎ፣ በመስኩ ዕውቀቱ ባላቸው ኢትዮጵያዊን ወጣቶች በተከናወኑ ተግባራት በራስ አቅምፍሬ አፍርቶ 8 በሚሆኑ የፌደራል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙከራ ትግበራ ተካሂዶ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል።
በዛሬው ዕለትም የውጤቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ከሆነው የባንክ ኢንዱስትሪ በባንኮች ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ አስተባባሪነት፥ ከ16 የባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር ስራው የደረሰበት ደረጃና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ገንቢ ውይይቶች መካሄዳቸው ተገልጿል።
በቀጣይ 6 ወራት 30 ሚሊየን ዜጎችን የመመዝገብ ግብ እንዲሳካ ሁሉም ዜጎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.