Fana: At a Speed of Life!

አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ቅድሚያ ሰጥቶ ይሰራል የሚል እምነት አለኝ-ዶ/ር አረጋዊ በርሄ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ካለፈው በመማር የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ቅድሚያ ሰጥቶ ይሰራል የሚል እምነት አለኝ ሲሉ የትግራይ  ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፈ ምርጫ አካሂዳለች ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህም በመጪው መስከረም 24 በህዝብ ይሁንታ አግኝቶ በምርጫ ያሸነፈው አዲስ መንግስት ይመሰረታል ብለዋል።

ዶክተር አረጋዊ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አጋጥመው ከነበሩ የፖለቲካ ስህተቶች ብዙ ነገሮችን ይማርበታል ነው ያሉት።

በዚህም የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታትና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በቁርጠኝነት ይሰራል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።

የፊታችን መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ እንደሚሆን እናምናለን ነው ያሉት።

”መስከረም 24 የሚቋቋመው መንግስት በህዝቦች ፍላጎት የመጣ ስለሆነ ህዝቡ ቁጥጥር ሊያደርግበት ይችላል ማለት ነው።

እኛ የመረጥናችሁ ለዚህ ምክንያት ነው ይሄንን ተግባራዊ እያደረጋችሁ ነው ወይ ብሎ ሊጠየቅ የሚችል መንግስት ነው፡፡ ይሄ አዲስ መንግስትም ካለፈው ሂደታችን ትልቅ ትምህርት ወስዶ ህዝቡ የሚፈልገውን ነገር ያሟላል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።

በሰላማዊ የምርጫ ሂደት አልፎ መንግስት መመስረት ለቀጣዩ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ዶክተር አረጋዊ  ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አምኖበት የሰጠውን ድምፅ በማክበር የአገሪቷን መጻዒ ዕድል የተሻለ ማድረግም ከአዲሱ መንግስት የሚጠበቅ ስራ ነው ብለዋል።

‘’ይሄ ቀጣይ ጉዟችን የተረጋጋና ህዝብ የሚፈልገውን ነገር ተግባር ላይ እያዋለ የሚሄድበት አንድ ሽግግር ነው ለውጥ ነው።

ይሄ የለውጥ መንግስት ለውጥን አሁን ለውጥን በተረጋጋ ሁኔታ የሚያካሂድበት ዕድል ተሰጥቶታል በህዝቡ ስለዚህ ተገቢውን ውጤት ህዝቡ የሚጠብቀውን ውጤት እንደሚያሳይ ሙሉ ተስፋ አለኝ።’

በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውድድር ከተደረገባቸው 436 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች በ410ሩ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.