የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሃግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ መስከረም 20 የሚካሄደው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል ።
በዚህ ምርጫ የቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ጨምሮ የፓርቲውከፍተኛ አመራሮችና እጩ ተወዳዳሪዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሶማሌ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ የሶማሌ ብልፅግና በጅግጅጋ ከተማና ባጠቃላይ በክልሉ ያቀረባቸው ተወዳዳሪዎች እውቀት ፣ ልምድና አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል።
በጅግጅጋ ከተማ ባለፉት ሶስት አመታት ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የገለፁት ሀላፊው፥ በቀጣይም በከተማው የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አያይዘውም የብልፅግና ፓርቲ የክልሉን ህዝብ አንድነት ፤ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ጠቁመው፥ የከተማው ነዋሪዎች ብልፅግናን በመምረጥ የከተማውንና የክልሉን ብልፅግና ለማሳካት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሀግብሩ ላይ የተገኙ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች፥ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 27 አመታት ያልተሰሩ በሶስት አመታት ውስጥ በከተማው በርካታ የልማት ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል።
በመስከረም 20 በሚካሄደው ምርጫ ብልፅግናን ለመመረጥ መዘጋጀታቸውን የገለፁት የከተማው ነዋሪዎች፥ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ መናገራቸውን ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!