Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ ዐቢይ ንግግሮች እና መግለጫዎችን ያካተቱ ሦስት ጥራዞች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ዛሬ በተለያዩ መድረኮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተናገሯቸውን ንግግሮች እና መግለጫዎች ያካተቱ ሦስት “ከመጋቢት እስከ መጋቢት ” የተሰኙ ጥራዞች ይፋ አደረገ።
ንግግሮቹ እና መግለጫዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሶስት አመታት በሀገራዊ ፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን እሳቤ አቋም የሚያንፀባርቁ ናቸው።
የፊታችን መስከረም 24 ቀን 2014 በኢትዮጵያ ከሚደረገው አዲስ የመንግሥት ምስረታ ቀደም ብሎ የቀረበው ይህ ስብስብ በመጋቢት 2010 የመንግስት ሽግግር ከተደረገ በኋላ በተደረጉ ንግግሮች እና መግለጫዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተተገበሩ የተለያዩ ቁልፍ የመንግስት ሥራዎችን በታሪክ ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+7
0
People Reached
234
Engagements
Boost Post
216
14 Comments
4 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.