Fana: At a Speed of Life!

የሜ/ጀ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማዕረግ ዕድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሜ/ጀ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስራ አፈጻጸም ብልጫ ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ ።
ከከፍተኛ መኮንን እስከ ባለ ሌላ ማዕረግ ለተሾሙ 75 የሰራዊት አባላት ፥ የክብር እንግዳ እና የህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀ ይመር መኮንን ፣ የኮሌጁ አዛዥ ኮ/ል አበበ ዋቅሹማ እንዲሁም የኮሌጁ ም/አዛዠ ለሰው ሀብት ኮ/ል አለማየሁ ሰበቡ ማዕረግ አልብሰዋል።
በዚሁ ወቅት የህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀ ይመር መኮንን እንደተናገሩት ፥ የማዕረግ ዕድገት ተጨማሪ የሀገር ሀላፊነት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በዚህ ተቋም እስከ 40 አመት በማገልገል እውቅና የተሰጣችሁ እኛም ከናንተ ተምረን ተቋማችንን በታማኝነት እስከመጨረሻው እናገለግላለን ብለዋል።
በዚሁ የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርዓት ላይ ከኮሌጁ በክብር የተሰናበቱ የሠራዊት አባላት እና ሲቪሎች ምስጋና እና እውቅና መሰጠቱን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
14
Engagements
Boost Post
12
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.