Fana: At a Speed of Life!

ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሥራ ላይ ተሰማርተው በተገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወቅታዊ ሁኔታዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኑሮ ውድነቱን ለማባባስ የሞከሩና የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጠሩ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሠይድ ሙሐመድ ፥እስካሁን ባለለው ሁኔታ ከ2000 በላይ የንግድ ድርጅቶች በምን ሁኔታ ላይ እየሰሩ እንደሆኑ የቤት ለቤት አሰሳ ተደርጓል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የሌላቸው፣ ህጋዊ የዋጋ ዝርዝር ያልለጠፉ፣ ያለአግባብ ምርት የከዘኑ፣ ለኑሮ ውድነቱ መባባስ ምክንያት የሆኑ ከ800 በላይ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡ 769 ድርጅቶች ታሽገዋል፡፡ 25 ድርጅቶች ተከሰው ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት ሄዷል፡፡
በዚህ ረገድ ጠንከር ያለ እርምጃ ተወስዷል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ሌላው እርምጃ በመውሰድና የንግድ ድርጅቶችን ወደ ትክክለኛው መንገድ ብቻ በማምጣት የማይፈታው የአቅርቦት ችግር መኖሩን የገለጹት አቶ ሰይድ፥ በአሁኑ ወቅት በርካታ ተፈናቃዮች በመኖራቸው የአቅርቦት ችግር ለማቃለል ምርት ካለበት አካባቢ መሠረታዊ የህብረት ሥራዎችን እና ዩኒየኖችን በመጠቀም ከፍተኛ መጨናነቅ ወደ ሚስተዋልባቸው ደሴ እና ኮምቦልቻ አካባቢዎች ምርት እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት 880 ኩንታል ጤፍ፣ 790 ኩንታል በቆሎ፣ 650 ኩንታል ማሽላ፣ 1ሺ220 ኩንታል የዳቦ ዱቄት እና 550 ሺህ ሊትር ዘይት ከሌሎች አካባቢዎች በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ገብቷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.