Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ አስተዳደር አዲሱ ምክር ቤት ነገ ይመሰረታል

አዲስ አበባ፣መስከረም 17፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር አዲሱ ምክር ቤት የሕዝቡን መሠረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ መደራጀቱን የአስተዳደሩ አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ አስታወቁ።
የድሬዳዋ አስተዳደር አዲሱ ምክር ቤት ነገ እንደሚመሰረትም ተገልጿል።
ድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ሁለተኛ የሥራ ዘመን 48ኛ መደበኛ የመጨረሻ ጉባዔ ዛሬ አካሂዷል።
አፈ ጉባዔዋ በወቅቱ በጉባኤው ላይ እንዳስታወቁት፤ አዲሱ ምክር ቤት የሕዝቡን ጥያቄዎች ትርጉም ባለው መንገድ ለመመለስ በጥናት የተደገፈ ተግባር ተከናውኗል።
በጥናቱ የተመለከተው አሠራርና አደረጃጀት ሙሉ አቅም የሚፈጥርና የህብረተሰቡን አንገብጋቢ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነት እንደሚመልስ የታመነበት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አዲሱ የሚዋቀረው አስተዳደር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ለመወጣት እንደሚያስችለው አፈ ጉባዔዋ ተናግረዋል።
እንዲሁም የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግም ጠቁመው፤ ድሬዳዋን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል ወይዘሮ ፈጡም።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ፤ የካቢኔ አባላት ለቀጣዩ ምክር ቤት በጥናት ተደግፎ የተዘጋጀው ሰነድ በተግባር ሲተረጎም ውጤት እንደሚመዘገብበት እምነታቸውን ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ የ47ኛው መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ በሙሉ ድምፅ አድድቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.