Fana: At a Speed of Life!

የምክር ቤቱን አሰራር የሚያሻሽሉ ዲጂታል መተግበሪያዎች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሰራርን የሚያሻሽሉ አራት ዲጂታል መተግበሪያዎች ይፋ ተደርገዋል።
መተግበሪያዎቹ መረጃን በቀላሉ ለመለዋወጥ የሚያስችሉ እና የተደራሽነት ችግርን የሚቀርፉ ናቸው ተብሏል።
መተግበሪያዎቹ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ በምክር ቤቱ የሚገኙ ቃለ ጉባኤዎች እና ሰነዶችን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናግረዋል፡፡
መረጃን ለማግኘት ይወስድ የነበረውን ጊዜ እና ገንዘብ የሚቆጥቡ፣ ህዝብ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ግንኙነትም የሚያጠናክሩ መሆናቸውንም አፈ ጉባኤው ገልጸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.