የሚበጀንን ፓርቲ መርጠናል- የሐረር ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ማልደን በመነሣት ለአምስት ዓመት የሚያስተዳድረንን ፓርቲ በዲሞክራሲያዊ መንገድ መርጠናል ሲሉ የሐረር ከተማ መራጮች ተናገሩ።
ዛሬ እየተካሄደ የሚገኘው ምርጫ ቀደም ባሉ ጊዜያት ከተካሄዱ ምርጫዎች ጋር ሲነጻጸርም የተሻለ እና ህዝቡም በራሱ ፈቃድ ያሻውን የመረጠበት መሆኑንም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የተናገሩት።
በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱም አንድም ጣልቃ የሚገባ ሰው የለም ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ÷ በነጻነት ለሚፈልጉት ፓርቲና ግለሰብ ድምጽ መስጠታቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደት እንደዚህ ያለ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ ከዚህ ቀደም አይተው እንደማያውቁም ነው የተናገሩት፡፡
በሐረሪ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን 229 የምርጫ ጣቢያዎችም አሉ፡፡
በዛሬው ዕለትም ከ147ሺ በላይ ሰዎች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!