Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል መንግስት የምስረታ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የሲዳማ ክልል መንግስት የምስረታ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በክልሉ ምክር ቤት የእለቱ ጉባዔ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተመረጡት 190ውም የሲዳማ ክልል ህዝብ ተወካዮች ህዝቡን በታማኝነት ለማገልገል ቃለመሃላ ይፈፅማሉ፡፡
እንዲሁም የሶስቱን የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጪ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈፃሚውን ይሰይማሉ፡፡
በተጨማሪም የክልሉን መንግሥት ካቢኔ ለማዋቀር የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የም/ቤት አፈ ጉባዔ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በርናባስ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.