Fana: At a Speed of Life!

የኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ለጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

መሪዎቹ በላኩት የደስታ መግለጫ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መልካም ምኞታቸውን አስፍረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአገራቸው እና ህዝባቸው ልማት እና ብልፅግና የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግቡም መልካም ምኞታቸውንም መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.