Fana: At a Speed of Life!

ዜጎች ከዚህ ያነሰ አገልግሎት አይገባቸውም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲሱ መንግሥት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዚህም ‘’በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በዚህ ሳምንት በሚኖራቸው የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና ወቅት፣ በአገልጋይ መሪነት ልብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ’’ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹትም÷ የዚህች ታላቅ ሀገር ዜጎች ከዚህ ያነሰ አገልግሎት አይገባቸውም ሲሉ መልእክታቸውን አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.