Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤን እውነቷን ለማሳወቅ ትጠቀምበታለች- አምባሳደር ዲና

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅና እውነቷን ለማሳወቅ ትእደምትጠቀምበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

አምባሳደር ዲናየስራ አስፈፃሚው ምክር ቤት ጉባኤ በዝግ የመከረባቸውን ጉዳዮች አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኮቪድ ተግዳሮቶች፣ የክትባት ሁኔታ፣ አፍሪካዊ የክትባት ፈጠራዎች መበረታታት፣ የአፍሪካ ህብረት በጀትን በራስ መቻል፣ ብክነትን በቀነሰ መልኩ በጀቷን ልትሸፍን ይገባል፣ የአፍሪካ ህብረት መዋቅርን ማስተካከል፣ የሚሉ አጀንዳዎች መቅረባቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በመታዘቡ ኢትዮጵያ ምስጋናዋን አቅርባለች።

በኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኩል ተብራርቷል፡፡

በአፍሪካ ህብረት የተለያዩ መዋቅሮች ሰዎችን መምረጥ፣ ሲዲሲን ማጠናከር ከሰዓት ውይይት እንደሚካሄድባቸው አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።

ቤኒን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ለመክፈት ፍላጎት እንዳላት መግለጿንም ቃለአቀባዩ ገልፀዋል።

ከስብሰባው ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ እውነታውን የማስረዳት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ያነሱት።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚል ጠንካራ አቋም ያላት መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ዲና÷ በዚህ መርህ እውነቷን በማሳወቅ ስብሰባውን እንደመልካም አጋጣሚ ትጠቀምበታለች ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.