ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ታዛዥ መንግሥት እንዲኖር ስለሚፈልጉ የንፁሃንን ጥቃት እንዳላዩ ማለፍ መርጠዋል – ዶ/ር አረጋዊ በርሄ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምዕራባውያንና መገናኛ ብዙሃናቸው በኢትዮጵያ ታዛዥ የሆነ መንግሥት የመመሥረት ፍላጎት ስላላቸው አሸባሪው ህወሓት በንፁሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እንዳላዩ ማለፍ መምረጣቸውን ዶክተር አረጋዊ ገለጹ።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ለኢፕድ እንደገለጹት÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሽብር ተግባሩን በመቀጠል ከሰሞኑ በአማራ ክልል ውጫሌ እና በአፋር ክልል ጭፍራ ላይ በርካታ ንጹሃንን ጨፍጭፏል።
ተላላኪ መንግሥት የመመስረት ዓላማ ያላቸው ምዕራባውያንና መገናኛ ብዙሃናቸው ይህንን የንጹሃን ጥቃት እንዳላየ ማለፍ መምረጣቸውን ጠቁመው ÷ መከላከያ ሰራዊት ቡድኑ ለጥፋት የሚጠቀምበትን የግንኙነት ጣቢያ ላይ እርምጃ ሲወስድ በንጹሃን ላይ ጥቃት ያደረሰ በማስመሰል ማራገብን መርጠዋል ብለዋል።
ምዕራባውያን በአንድ ወገን ሽብርተኝነትን እንዋጋለን ይላሉ በተግባር ደግሞ ሽብርተኝነትን እየደገፉ ኢትዮጵያ ነጻና ሉዓላዊት ሀገር ሆና ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት በማጨናገፍ ለእነሱ አሽከር የሆነ መንግሥት እንዲመሰረት እየሰሩ መሆናቸውን ዶክተር አረጋዊ ገልጸዋል፡፡
ይህን ሁኔታ ሰላም ወዳድ የሆነ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሁሉ ሊኮንነው የሚገባ ሸውራራ አካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!